Buzz Ethiopia

እኛ ማለት

 By Adoni Ado
★እኛ ማለት በ2008★

መንግስት 88 ኮንዶሚኒየሞች ጠፉብኝ ሲለን እግራችንን
ሰቅለን የሳቅን

የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ጋምቤላ ላይ በጥይት ሲፈጁን
ከመንግስት ቀድመን ብሔራዊ የሀዘን ቀን ያወጅን

ስለ እስራኤል መንግስት ሲወራ ክርስቲያን የተነካ
እየመሰለን ሙስሊም ወንድሞቻችንን የሰደብን
:
ስለ አረብ ሲወራ እስልምና የተነካ እየመሰለን ክርስቲያን
ወንድሞቻችንን ያስቀየምን
:
አባ ግርማ ከእስር እንዲፈቱ ዘመቻ የከፈትን

የሙስሊም ኮሚቶዎች ነፃ እንዲዎጡ የታገልን

ሶሪያ ውስጥ ህፃናት በቦንብ ሲጋዩ አይተን እንዳላየን ያለፍን

ፈረንሳይ በሽብር ጥቃት ምክንያት በጣት የሚቆጠሩ ሰዎች
ሲገደሉባት የፈረንሳይን ባንዲራ ለብሰን ስቅስቅ ብለን ያለቀስን

ሳውዳረቢያ የመንን በጦር አውሮፕላን ስታፈራርስ ምናገባን
ብለን ጭጭ ያልን

የማትሪክ ፈተና ተሰረቀ ሲባል የተገረምን…. ተገርመንም
ለሁሉም እንዲደርስ ሼር ያደረግን

ህዝባችን በኤሊኖ ምክንያት በረሀብ ሲገረፍ የተመለከትን
:
ኢሀአዲግ መቶ ፐርሰንት አሸንፌያለው ብላ ድምፃችንን
ስትቀማን ድምፅ አልባ የሆንን

እኛ ሰፈር ውሀ ለአንድ ሳምንት ስጠፋ ሮቤል ኪሮስ ግን ብራዚል
ድረስ ሄዶ ገላውን ሲታጠብ አይተን የታዘብን

ሉሲ ከዛፍ ላይ ወድቃ ነው የሞተችው ሲሉን በሳቅ
የተንፈራፈርን

የኦሮሚያን እና የአማራን አመፅ የደገፍን… በሞቱት
ወንድሞቻችን ክፉኛ ያዘንን

በቻት የተዋወቅን…. የተጀናጀንን… የተጣበስን

ሲሻን ኢትዮጲያዊ አንድነትን የሰበክን ሲሻን ደግሞ
በየኮሜንቱ በዘር፣ በሀይማኖት እና በጎሳ ተከፋፍለን የተሰዳደብን

እኛ ማለት የገዛ ጠ/ሚኒስትራችን በገዛ ፍቃዱ መሳሪያ አስተኩሶ ያገሩን ልጅ ሲያስጨርስ ያየን
እኛ ማለት የታሰሩ ወንድሞቻችን በእሳት ሲቃጠሉ እኛ
ጨጓራችን የተጠበስን
እኛ ማለት…… ከ2008 እሳት ተርፈን ለ2009 ልንደርስ
የተዘጋጀን ፌስቡካውያን ነን፡፡