የአስተሳሰብ ጓደኛ ስለማፈላለግ የወጣ ማስታወቂያ

መስፈርት፥
ዜግነት———-ኢትዮጵያዊ
የጤና ሁኔታ———–በ ኢቦላ ያልተያዘ/ች
እድሜ———–18-30
ፆታ—————አይለይም
ቁመት*ክብደት———አይለይም
የት/ት ደረጃ————-መፅሀፈ ህሊናውን/ዋን እና ይህንን ፅሁፍ ለማንበባ የበቃ/ች/
ሌሎች————–አሳማኝ ሀሳብ ሲገኝ የሚያምን/የምታምን እንዲሁም ጥሩ ሀሳብ አምጥቶ የሚያሳምን/አምጥታ የምታሳምን፣ ከጫማ ሽታ፣ከ homosexuality፣ከዘረኝነት፣ ከጨለምተኝነት፣ከባርነት ነፃ የሆነ እንዲሁም ከታች ያሰፈርኩትን ፅሁፍ አንብቦ/አንብባ *ፈጣሪ ይቅር ይበልህ!* ያላለ/ያላለች።

እምነቴ ነፃነት ይባላል፡የነፃነት ተከታይ ነፃ ይባላል፡ቅዱስ መፅሃፌ ህሊና ይባላል፡ ሰው አክብራለሁ፡ አልሰርቅም፡ ተፈጥሮን አደንቃለሁ፡ ሙዚቃን እወዳለሁ፡ የሁሉም ጤነኛ ሰው ህሊና ንፁህ እና ሁሌም ትክክል ነው ብዬ አምናለሁ፥ ታድያ ሰዎች ጥሩ ያልሆነ ተግባር የሚፈፅሙት ህሊናቸውን ነፃ አድርገው ስለማያሰሩት ወይም መፅሃፈ ህሊናችውን ማንበብ ስላቆሙ ነው ብዬ አምናለሁ፡አልሰብክም አልሰበክም፡ መንፈሳዊው አለም ቅዥት ነው ብዬ አምናለሁ፡ ሴጣን, ምናምን ብለን የምንጠራቸው ገፀ ባህርያት ምናልባት በሰው ልጅ ታሪክ ሂደት ብዙ እውቅና ያገኙ characters ናቸው ብዬ አምናለሁ፡ ሀገሬን እወዳለሁ፡ እናቴን እወዳለሁ፡ ለፍቅር ታላቅ ቦታ ሰጣለሁ፡ ሁለት ነገሮችን አንድ ስለሚያደርገው ሀይል ሁሌ እደመማለሁ፥ የምር እደነቃለሁ-እስቲ አስቡት ኤሌክትሮንን ከ ከፕሩቶን፣ አቶምን ከ አቶም፣ ሞለኪዩልን ከሞለኪዩል፣ ጨረቃን ከመሬት፣ መሬትን ከፀሃይ፣ ሰውን ከሰው፣ (ዱባለን ከዱባለች—-just 4 fun!) ብቻ ይህ ዩኒቨርስ ብዙ ሆኖ ሳለ አንድ ያደረገው አንድ ታላቅ ሀያል ሀይል(ENERGY)አለ ብዬ አምናለሁ።ታድያ ይህ ታላቅ ሀያል ሀይል የሰው ልጅ በታሪክ ሂደት ያፀደቀው እከሌ የተባለው ገፀ ባህርይ ሳይሆን ሁሉን የሚያሸንፈው፣ ከልብ ድረስ ዘልቆ የሚገባው፣ ሰውን የሚለውጠው፣ ብዙ የተባለለት ፍቅር ራሱ ይመስለኛል-በቃ ዝም ብሎ ይመስለኛል። ፍቅር emotion ነው ፣ፍቅር energy ነው(**ፍቅር matter ነው**(E=mc2)-just 4 fun!)፣ ፍቅር chemical bond ነው፣ ፍቅር በተለየዩ ቦታዎች በተመሳሳይ ጊዜ በአንዴ መገኘት ይችላል። ፍቅር አይሞትም፣ ፍቅር ስገዱልኝ-አምልኩኝ አይልም፣ ፍቅር አይቆጣም-አይቀጣም፣ ፍቅር ወደ ገሀነም አይጥልም-በ ምድራዊ ገነት ያኖራል እንጂ፣ ፍቅር አይሰበክም ምክንኛቱም በሁሉም ሰው ልብ ውስጥ አለና፣ ፍቅር ሰው ግደሉ አይልም ምክንኛቱም ፍቅር ነውና፣ ፍቅር አይናገርም ምክንኛቱም ህይወት የሌለው ነገር ግን ህይወት የሚሰጥ ነውና። ፍቅር ከላይ የጠቀስኳችውን ባህርያት ቢኖሩትም እንኳ ፈጣሪ ነው ለማለት ምንም አይነት proof የለኝም። እግዚኣብሔር/አላህ—-ያልነበሩ እና የሌሉ ገፀ ባህርያት ናቸው ምክንኛቱም sense አይሰጥም –ማለት በ ሀሊናዬ ውድቅ ተደርጓል።

ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት የምታሙዋሉ—FB request-አድርጉልኝ በደስታ እቀበላችኌለሁ::

ከላይ የሰፈረው ጽሁፍ ከመፅሀፈ ህሊና ምዕራፍ ፩ የተወሰደ ነው።

***(ትርጉም–ህሊናዬ skull በተባለ አጥንት ስር ባለ Neural Network ውስጥ ያለ ይህንን ፅሁፍ ከራሱ በራሱ ወደ እናንተ ለማድረስ የእጆቼን intrinsic ጡንቻዎች እያዘዘ ያለ መረጃ ነው። ፍቅር በ ህሊናዬ ውስጥ ሁሌም ይኖራል ምክንኛቱም ህሊናዬ የ neuronoቼ ፍቅር ውጤት ነውና።)

ህሊናችሁ ማስተዋል፣ መረጋጋት ከማጣት እንዲሁም ሳያነቡ እና ሳይረዱ comment ከማድረግ ይጠብቃችሁ::
አሜን!