ደውዬ ነበር!

By Assaye Derbie  'ደውዬ ነበር፡፡
(አሳዬ ደርቤ)
ስልኩን ያነሳችው ሴት አንደበቷ ይለሰልሳል፡፡
‹‹ምን ነበር?›› አለችኝ፡፡
‹‹ትዳር ፈልጌ ነበር!›› አልኳት፡፡
‹‹ምን አይነት ሴት ነው የምትፈልገው?›› በማለት መለሰችልኝ፡፡
‹‹ድንግልና ያላት›› ብላት ‹‹አይሻልህ ዳይኖሰር ያላት›› ብላኝ ስልኩን ጆሮዬ ላይ ስለምትዘው ‹‹እጃችሁ ላይ ያሉት ሴቶች ምን ምን አይነት ናቸው?›› አልኳት፡፡
‹‹እኛ ብዙ አይነት ሴቶች አሉን››  
‹‹እኮ ምን ምን አይነት?›› አልኳት ‹‹ሴቶች ሁሉ አንድ አይነት ናቸው›› ያለኝን የጓደኛዬን ምክር እያስታወስኩ፡፡
‹‹ቆይ አንተ ለትዳር የምትፈልገው ተማሪ ነው ወይስ የራሷ የሆነ ስራ ያላት?››
‹‹የራሷ የሆነ ጸጉር ይኑራት እንጂ ተማሪም ብትሆን ግድ የለኝም››
‹‹ኦኬ… እንደዚያ ከሆነ በውበታቸውም ሆነ በጸባያቸው የተመሰከረላቸው ሶስት ቆንጆ ትዳር ፈላጊ የኮሌጅ ተማሪዎች አሉን›› በማለት ስለ ቅርጻቸው ሸንቃጣነት፣ ስለ ቆዳቸው ጥራት፣ ስለ ፊታቸው ደም-ግባት በሰፊው ስታብራራልኝ የቤቴ ጥበት እና የደሞዜ ጥቂትነት ባይገድብኝ ኖሮ ‹‹አፈር ስሆን ሶስቱንም ዳሪልኝ!›› ማለቴ አይቀርም ነበር፡፡
ሆኖም ግን ከሶስቱ አንዷን መምረጥ ስለነበረብኝ ‹‹እስኪ ስለሚለያዩበት ነገር ንገሪኝ›› አልኳት፡፡
‹‹በምንም አይለያዩም! ሶስቱም በሚባል መልኩ በባህሪያቸው ታጋሽ፣ በቁንጅናቸው ሸጋ የሚባሉ ናቸው፡፡››
‹‹እድሜያቸውስ ስንት ስንት ነው?›› አልኳት በእድሜያቸው እንኳን ቢበላለጡ ብዬ፡፡
‹‹ሶስቱም አስራ ስምንት አመታቸው ነው!›› አለችኝ፡፡
‹‹መንትያ ናቸው እንዴ?››
‹‹እንግዲህ አቶ አሳዬ እኔ የምነግርህ ፕሮፋይላቸውን እያነበብኩ ነው፡፡ እንደሚታየኝ ከሆነ የሰጠናቸው ፎርም ላይ የሞሉት 18 አመት ብለው ነው!›› አለችኝ፡፡
ለነገሩ ልፋ ቢለን እንጂ ሴቶቻችን ትክክለኛ እድሜያቸውን ከሚናገሩ ይልቅ ከሕይወት ዘመናቸው ላይ ‹‹በቁጥር›› የቀነሱት እድሜ ‹‹በተግባር›› ቢጎመድ ይሻላቸዋል፡፡ ያም ሆኖ የውልደት ሰርቲፊኬታቸውን ፍጡር የማይደርስበት ስፍራ ስለሚደብቁት እድሜያቸውን ቢዋሹም ችግር የለውም፡፡ እኔን የሚያናድደኝ ልጅ እያለን ‹‹በእልልታ›› የሾምነው መንግስት ወጣት ሆነን ‹‹በዋይታ›› ውረድ ስንለው ልክ እንደ ሴቶቻችን ከስልጣን ዘመኑ ላይ አስር አመቱን ጎምዶ… በኮልታፋ አንደበቱ ‹‹ባለፉት አስራ አምስት አመታት›› ማለቱ ነው፡፡ 
(ማሳሰቢያ፡- ከላይ ያለውን አረፍተ ነገር የጨመርኩት ነገሩ ስለተገጣጠመብኝ እንጂ ባንድ አረፍተ ነገር ሁለት አይነት እስር ማስተናገድ ፈልጌ አይደለም፡፡ የጽሑፌም ዋና ትኩረት በቀለበት ስለመታሰር እንጂ በካቴና ስለመታሰር አይደለም፡፡)
.
ወደ ሃሳቤ ስመለስ ከሶስቱ ሴቶች አንዷን መምረጥ ስለነበረብኝ… በዚህ እንኳን ቢለያዩ በማለት ‹‹እኒህ ሴቶች ለትዳር የሚፈልጉት ወንድ ምን አይነት ነው?›› አልኳት፡፡
‹‹ይቅርታ የደንበኞቼን መስፈርት በዝርዝር ከመናገሬ በፊት ስለ እርስዎ አንዳንድ ነገሮች ማወቅ ይኖርብኛል!›› አለችኝ፡፡
‹‹ለምሳሌ ምን ማወቅ ትፈልጊያለሽ?›› 
‹‹ማለቴ ስላሉህ ነገሮች››
‹‹ዌል እንግዲህ በመጀመሪያ ደረጃ የተሟላ ስራ እና ጤና እንዳለኝ ልነግረሽ አፈልጋለሁ፡፡››
‹‹እሽ!››
‹‹በመቀጠል አለኝ የምለው ነገር ‹ብሔር› ሲሆን…..››
‹‹ወንድሜ ደንበኞቼ ስለ ባሕሪህ እንጂ ስለ ብሔርህ የሚጨነቁ አይደሉም፡፡››
‹‹እንደዚያም ካልሽ ዋንጫ አግኝቼበት አላውቅም እንጂ በባህሪዬም ምስጉን ነኝ፡፡››
‹‹እሽ የራስህ የሆነ መኖሪያ ቤትስ አለህ?››
‹‹እጣው አልወጣልኝም እንጂ ባለ ሁለት መኝታ ቤት ኮንዶሚንዬም ተመዝግቤያለሁ፡፡››
‹‹መኪናስ?››
‹‹መንጃ ፍቃድ የማወጣበት ገንዘብ ስላላገኘሁ…..›› ንግግሬን አቋረጠችኝ፡፡
‹‹ይቅርታ! ደንበኞቼ ሊያገቡት የሚፈልጉት ወንድ በትንሹ የራሱ የሆነ ቤት እና መኪና እንዲኖረው ይፈልጋሉ፡፡››
‹‹መኪናና ቤት ከሌለኝስ?››
‹‹ከሌለዎትማ 8104 ላይ ከመደወልዎ በፊት 8100 ላይ ‹‹ኤ›› ብለው በመላክ እድልዎን መሞከር ይኖርበዎታል ማለት ነው››
ጢን፣ጢን፣ጢን 
ስልኩ ተዘጋ፡፡ 
(ሴቶቻችን ግን እኛ ለትዳር ስንፈልጋችሁ ከፍቅር በፊት ገንዘብን የምታስቀድሙት እስከ መቼ ድረስ ነው?››'

ደውዬ ነበር፡፡

(ሴቶቻችን ግን እኛ ለትዳር ስንፈልጋችሁ ከፍቅር በፊት ገንዘብን የምታስቀድሙት እስከ መቼ ድረስ ነው?››