የፓርቲ ልሳኖችን ይወቋቸው
(አፈንዲ ሙተቂ)
——
በኢትዮጵያ ታሪክ የታዩት ቀደምት የፖለቲካ ድርጅቶችና አሁን በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙት ፓርቲዎች አቋማቸውን የሚገልጹባቸውን ጋዜጦችና መጽሔቶች ታውቋችሃላችሁ…? ካላወቋችኋቸው እኚሁላችሁ፡፡
—–
1. “ሰርቶ አደር” ጋዜጣ- የኢትዮጵያ ሰራተኞች ፓርቲ (ኢሰፓ) ልሳን
2. “መስከረም” መጽሔት- የኢሰፓ የንድፈ ሃሳብ መጽሔት
3. “ሳገም” መጽሔት – የህዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ (ህግሓኤ) ልሳን
4. “ሀዳስ ኤርትራ” ጋዜጣ- የህዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ (ህግሓኤ) ልሳን
5. “ወይን” ጋዜጣ- የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ልሳን
6. “ዲሞክራሲያ” ጋዜጣ- የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) ልሳን
7. “የሰፊው ህዝብ ድምጽ” ጋዜጣ- የመላው ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን) ልሳን
8. “በከልቻ ኦሮሚያ” ጋዜጣ- የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ልሳን (በአማርኛ የሚታተም)
9. “ሰገሌ ቦሶና” መጽሔት- የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ልሳን (በኦሮምኛ የሚዘጋጅ)
10. “ኦሮሚያ” ጋዜጣ- የኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ልሳን
11. “አብዮታዊ ዲሞክራሲ” ጋዜጣ- የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ልሳን
12. “አዲስ ራዕይ” መጽሔት- የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) የንድፈ-ሃሳብ መጽሔት
13. “ማህቶት” ጋዜጣ- የብሄረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ልሳን
14. የደቡብ ድምጽ- የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ልሳን
15. “ሄጀሶት” ጋዜጣ- የሀረሪ ብሄራዊ ሊግ ልሳን
16. “ትውልድ” ጋዜጣ- የኢትዮጵያዊያን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ልሳን (አሁን በህትመት ላይ መኖሩን እንጃ)
17. “አንድነት” ጋዜጣ- የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ልሳን
18. “ፍኖተ ነጻነት” ጋዜጣ- የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ልሳን
19. “ነገረ ኢትዮጵያ” ጋዜጣ- የሰማያዊ ፓርቲ ልሳን
——-
ከነዚህ ጋዜጦችና መጽሔቶች መካከል የአንዳንዶቹ ህትመት ቆሟል፡፡ አንዳንዶቹ ግን ዛሬም ድረስ ይታተማሉ፡፡
ቸር ያቆየን፡፡
አፈንዲ ሙተቂ
ሚያዚያ 26/2006
—-
Afendi Muteki is a researcher and author of the ethnography and history of the peoples of East Ethiopia. You may like his facebook page and stay in touch with his articles and analysis: Just click the following link to go to his page.
https://www.facebook.com/afendimutekiharar